- Advertisement -Newspaper WordPress Theme
ስነ ፍጥረትከዳርዊኒዝም ተጻራሪ ሳይንሳዊ ምልከታ

ከዳርዊኒዝም ተጻራሪ ሳይንሳዊ ምልከታ

ከ አለማችን ከተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ በሺህ የሚቆጠሩ ዶክቶራል ሳይንቲስቶች አንድ የጋራ መግለጫ ላይ የፈረሙ ሲሆን በዚህ መግለጫቸው በ ዳርዊን ዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ያላቸውን አመለካከት አስፍረዋል። በዚህም መግለጫቸው ላይ አሁን ላይ ለምናያቸው የስነ ፍጥረት ረቂቅነት  የዳርዊን ዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ሊገልጽ ወይም ሊያስረዳ እንደማይችል ነገር ግን በ  ይህንን ጽንሰ በማስረጃዎች በ አንክሮ ልንመረምረው እንድሚገባ ነበር።

“We are skeptical of claims for the ability of random mutation and natural selection to account for the complexity of life. Careful examination of the evidence for Darwinian theory should be encouraged.” “There is scientific dissent from Darwinism. It deserves to be heard.”

 https://dissentfromdarwin.org/about/

እነዚህ ሳይንቲስቶች በ ዓለማችን ዕውቅ በሆኑት ዬል፣ ኤም አይ ቲ፣ ቱሌን፤ራይስ፣ ኤሞሪ፤ጆርጅ ሜሰን፣ ሊሃይ፤ ካምብሪጅ፣ ኦክስፎርድ፣ ስታንፎርድ፤ ከካሊፎኒያ ዩኒቨርሲቲ እና በመሳሰሉት ዩኒቨርሲቲዎች በተመራማሪነት እና በፕሮፈሰርነት ያሉ ሲሆኑ  ፤ ይህን መግለጫ ከፈረሙት መካከልም በ አለማችን ምርጥ 50 ከሚባሉ ሳይንቲስቶች መካከል ይገኙበታል። ለምሳሌ ያህል የሴንተቲክ ኦርጋኒክ ኬሚስት እንዲሁም የናኖ ቴክኖሎጂ ምሁር እንዲሁም ዕውቅ በሆነው ራይስ ዩኒቨርሲቲ የ ናኖስኬል ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ማዕከል የ መካኒካል ኢንጂኒየሪንግ፣ ማቴርያል ሳይንስ እና ኮምፒዩተር ሳይንስ ፕሮፌሰር የሆኑት ጄምስ ቱር ፤  በአለማችን በከፍተኛ ቁጥር ምርምራቸው እንደ ማጣቀሻ ሆኖ በሌሎች ሳይንቲስቶች የተጠቀሱ የቲዎረቲካል እና ኮምፒዩቴሽናል ኬሚስት እንዲሁም የ ፕርዱ ዪኒቨርሲቲ ፕሮፈሰር እና በዩኒቨርሲቲ ኦፍ ጆርጂያ የሚገኘው የኮምፒዩቲሽናል ኬሚስትሪ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት  ሄነሪይ ሼፈር ፤ በዬል ዩኒቨርሲቲ  የሴሉላር እና ሞለኪዩላር ፊዚዮሎጂ ፕሮፌሰር የሆኑ ፍሬድ ፊግዎርዝ እና የመሳሰሉት ይገኙበታል።

“የዳርዊን ዝግመተ ለውጥ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ያለው ዘዴ ተጠቅሞ ረቂቅ የሆነ ስነፍጥረትን ሊያስገኝ የሚችል አንድም ሳይንቲስት ባለመኖሩ ሁሉም ሳይንቲስቶች በዚህ ጽነሰ ሐሳብ ጥርጣሬያቸውን ሊያነሱ ይገባል።”

የባዮሎጂክ ተቋም ዳይሬክተር የሆነውና የስነፍጥረት ሳይንቲስት የሆነው ዳግላስ አክስ

“እንደ ባዮኬሚስት ተመራማሪነቴ እጅጉን በተወሳሰበው የጄነቲክ ኮድ እና እጅጉን ምጡቅ በሆነው የኮድ እና ዲኮድ አደራረግ እውነታ ስመልከት የዳርዊን ጽንሰ ሐሳብ ላይ ጥርጣሬ አደረበኝ።”

 ዶ/ር ማርከስ ኤበርሊን፣ የቶምሰን ማስ ስፔክቶሜትሪይ ላብራቶሪ መስራች እና የ ብራዚል ብሔራዊ ሳይንስ አካዳሚ አባል የሆነው።

ነገር ግን በሚዲያዎች እና በመጽሃፍቶች ላይ የሚስተጋቡት አሳዛኝ ዕውነታ ግን ሁሉም ሳንቲስቶች እና ተመራማሪዎች የ ዝግመተ ለውጥ ጽነሰ ሐሳብ የስነፍጥረት ረቂቅነት ሊያስረዳ እንደሚችል እንደሚያምኑ እና ሀቅ እንደሆነ ነው። በዘመናዊው የትምህርት ስርዓት ያለፍን ወይም ያለን በመጽሃፍቶቻችን ላይ የምንመለከታቸው ነገሮ አስረግጠው የሚናገሩት የዳርዊኒዝም ጽንሰ ሐሳብ ሙሉ በሙሉ በምሁራኖች ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው እና ተጻራሪ አስተሳሰብ ወይም የምርምር ውጤት ያለው አንድም ሳይንቲስት እንደሌለ ነው። በዚህም በዓለማችን ዙርያ ያሉ ብዙ ወጣቶች በዚህ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ጥያቄ እንዳያነሱ ወይም እንዳይጠራጠሩ አይምሯቸው አስቀድሞ ተቃኝቷል።

በዘመናዊው የትምህርት ስርዓት ያለፍን ወይም ያለን በመጽሃፍቶቻችን ላይ የምንመለከታቸው ነገሮ አስረግጠው የሚናገሩት የዳርዊኒዝም ጽንሰ ሐሳብ ሙሉ በሙሉ በምሁራኖች ዘንድ ተቀባይነት እንዳለው እና ተጻራሪ አስተሳሰብ ወይም የምርምር ውጤት ያለው አንድም ሳይንቲስት እንደሌለ ነው። በዚህም በዓለማችን ዙርያ ያሉ ብዙ ወጣቶች በዚህ ጽንሰ ሐሳብ ላይ ጥያቄ እንዳያነሱ ወይም እንዳይጠራጠሩ አይምሯቸው አስቀድሞ ተቃኝቷል።


ለተጨማሪ ዝርዝር ይህንን ይጫኑ

Subscribe Today

GET EXCLUSIVE FULL ACCESS TO PREMIUM CONTENT

SUPPORT NONPROFIT JOURNALISM

EXPERT ANALYSIS OF AND EMERGING TRENDS IN CHILD WELFARE AND JUVENILE JUSTICE

TOPICAL VIDEO WEBINARS

Get unlimited access to our EXCLUSIVE Content and our archive of subscriber stories.

Exclusive content

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme

Latest article

More article

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme