- Advertisement -Newspaper WordPress Theme
የእግዚያብሔር ቃልእስከ መጨረሻ መወደድ ለተስፋ

እስከ መጨረሻ መወደድ ለተስፋ

እግዚአብሄር ዓለምን ከመውደዱ የተነሳ አንድ እና ብቸኛ ልጁን አሳልፎ በመስጠት በእርሱ የሚያምን ሁሉ ለዘላለም ህይወት እንጂ እንዳይጠፋ ፈቀደ:: ዩሃ 3:16 ዓለምን ሁሉ ከእግዚአብሄር የለየ ችግር ተፈጥሯል አንድ ጊዜ::

ሰው ሁሉ ከእግዚአብሄር ተለየ ማለት ደግሞ ጠፋ ወይም ተንከራታች ብኩን እና ከንቱ ሆነ ማለት ነው:: ከእግዚአብሄር ጋር ደግሞ ህብረት ለማድረግ ተገቢውን ቅድመ ሁኔታ ማሟላት ግዴታ ይሆናል:: ቅድመ ሁኔታው ግን በእራሱ በእግዚአብሄር ልክ ለእራሱ ለእግዚአብሄር የሚቀርብ ካልሆነ ምንም የሚመጥን አይሆንም::

ነገር ግን ደግሞ እግዚአብሄር ዓለምን የሰው ልጅን ስለሚወድ እና የፍቅር አምላክ ስለሆነ በሚመጥን ስምምነት ህብረቱን ለማስቀጠል ፈቀደ:: ስምምነቱ ባለ ሁለት አንቀፅ ነበረ:: የፍርድ አንቀፅ እንዲሁም የምህረት አንቀፅ:: ትልቅ መስዋዕትን ከስጦታ ጋር የሚያቀርብ ስምምነት:: ፍርድን እና ምህረትን በአንድ ላይ የሚፈፅም ስምምነት! አንድ ብቻ ልጅ:: ብቸኛ ልጁን መስጠት እና መሰዋት ነበረበት እግዚአብሄር::

ዓለምን ስለወደደ እግዚአብሄር እንደ ብርሃን ለዓለም ሁሉ አብርቶ የሚሰዋ መስዋዕት ሆነ ወልድ:: አባት እግዚአብሄር ጨከነበት:: እግዚአብሄር ነፍሱን የሃጥያት መሰዋዕት አደረገው:: መድቀቁ አና መሰቃየቱ የእግዚአብሄር ፍቃድ ነበር:: የሁላችንምበደል በእርሱ ላይ ተጫነበት:: ይህ ቅጣት ፍርድን አስፈፀመ:: ይህ ብቸኛ ልጅ ከዚህ ሁሉ ቅጣት በኃላ ምህረትን ስጦታን እና ሁለተኛ እድልን ለሰው ሁሉ ልጆች እንኾኝ ብሎ መርቆ ከፈተ:: በእርሱ ህይወትነት ብቸኛም መንገድነት ያመነን በዘላለም ህይወት እና በህያው ህብረት አንበሸበሸው:: አይጠፋም:: ለዘላለም ይኖራል:: ይህን ማን ያምናልስ ማንስ ያስተውላል?! እነሆ የዘላለም ህይወት ተስፋ….

Subscribe Today

GET EXCLUSIVE FULL ACCESS TO PREMIUM CONTENT

SUPPORT NONPROFIT JOURNALISM

EXPERT ANALYSIS OF AND EMERGING TRENDS IN CHILD WELFARE AND JUVENILE JUSTICE

TOPICAL VIDEO WEBINARS

Get unlimited access to our EXCLUSIVE Content and our archive of subscriber stories.

Exclusive content

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme

Latest article

More article

- Advertisement -Newspaper WordPress Theme